Friday, October 22, 2010

መገናኛ ተባእት

ስኬታማ ሲሆን ወንዱን ያወጡታል
'ጠንካራ ሴት አለች ከጀርባው' ይሉታል
ሴትም ደስ ይላታል ሸንጎ ሲቀባባት
'ረዳት ነሽ' ማለት ምስጢሩ ርቆባት
ቆማ እንደማትሄድ በራሷ ጎዳና
ማጀት እንድትባጅ ጥንት ተፈርዷልና
ፊት መሪ እንደማትሆን ይነግሯታል አሉ
ጋዜጠኛና ባል እየተማማሉ

ፍርደ ገምድሉ አለም አያልቅም ምጸቱ
ለልበ-ሙሉ ሴት ተዛብቶ አንደበቱ
ስኬታማ ስትሆን ሴትም በፈንታዋ
'ጠንካራ ወንድ አለ መቼም ከጀርባዋ'
ብሎ ይታበያል ወንዳወንዱ ሸንጎ

'ራሷን አትችልም' ከሚል አዘቅት ሰርጎ


2 comments:

  1. Interesting! you came back almost after one year to post such a very nice piece of work. Welcome back!

    ReplyDelete